Play all audios:
ፖለቲካጀርመንየአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ 4 መጋቢት 2017ሐሙስ፣ መጋቢት 4 2017 የአውሮጳ ኅብረትን የንግድ ፖሊሲ የሚመራው የኅብረቱ ኮሚሽን እንዳለው አሜሪካን በብረት እና በአሉምንየም ላይ ለጣለችው የ25 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ፣ ኅብረቱ ከጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ አንድ
አንስቶ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰድ ይጀምራል ብሏል።
https://p.dw.com/p/4rkI5የአዉሮጳ ህብረት አርማ ምስል፦ Nick Gammon/AFP/Getty Imagesማስታወቂያየአውሮጳ ሕብረት አጸፋዊ ምላሽ To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that
supports HTML5 audio
የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ አሜሪካ ከትላንት ጀምሮ በብረት እና በአሉምንየም ምርቶች ላይ ተግባራዊ ለምታደርገው አዲሱ ታሪፍ፣የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል። የአውሮጳ ኅብረትን የንግድ ፖሊሲ የሚመራው የኅብረቱ ኮሚሽን እንዳለው አሜሪካን
በብረት እና በአሉምንየም ላይ ለጣለችው የ25 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ፣ ኅብረቱ ከጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ አንድ አንስቶ የአጸፋ ርምጃዎችን መውሰድ ይጀምራል ብሏል። የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን ከአጸፋ ርምጃው ጋር፣ ኅብረቱ ለድርድር ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።በጉዳዮ ላይ
ከብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ የማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንድታደምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።ገበያው ንጉሴዮሃንስ ገብረእግዚአብሄርእሸቴ በቀለ
መጋቤ ምላሽዎን ይላኩልንየርስዎ መጋቤ ምልሽ